አስተያዬት ሰጪዎች


የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

የአክሰስ ሪል ኤስቴት ቤት ገዢዎች ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው ሰባት አባሎች ያሉት የአሪኤቤገማ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ቀጥሉ የማኅበሩ የበላይ አካል ሲሆን የማኅበሩን ሥራዎች የማስፈጸም ሓላፊነት ያለበት አካል ነው።

ፕሮፌሰር ጥላሁን ተካ ወልዴ

ቤት ገዢ፣ ቦሌ ጃፓን ሳይት እንዲሁም የአክሰስ ሪል ኤስቴት ቤት ገዢዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት

ፕሮፌሰር ጥላሁን ተካ እና ዶ/ር ቤተልሄም ተኮላ ከአክሰስ ሪል ኤስቴት አክሲዮን ማኅበር እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቦሌ-ጃፓን አፓርትመንት ውስጥ በሚገኝ ኮንዶሚኒየም ህንፃ ውስጥ ባለ 111 ካሬ ሜትር ባለ ሶስት መኝታ ቤት ለመግዛት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን አክሰስ ሪል ኤስቴት አክሲዮን ማኅበርን በመወከል የፈረሙት አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ናቸው።